በDC Health Link አማካኝነት HealthCare4ChildCare፦
ለቅድመ ልጅነት ትምህርት አቅራቢዎች እና ቡድኖቻቸው ተመጣጣኝ የሆነ የጤና ሽፋን
በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የልጅ እድገት ማዕከላት ወይም ቤቶች አሰሪ ለሆኑ ሰዎች HealthCare4ChildCare
HealthCare4ChildCare (HC4CC) ለአሰሪዎች በDC Health Link በኩል በመጀመሪያ የልጅ እድገት ማዕከላት ወይም ቤቶች ውስጥ አሰሪ ለሆኑ ሰዎች (እና ሰራተኞቻቸው) እና በኦፊስ ኦፍ ዚ ስቴት ሱፐርኢንተንደንት ኦፍ ኤጁኬሽን) ፈቃድ ለተሰጣቸው ነጻ ወይም ዝቅተኛ ወጪ ያለው የጤና መድን ያቀርባል።
- አሰሪዎች በወርሃዊ ፕሪሚየሞች $0 መክፈል ይችላሉ (ለተጨማሪ ዝርዝሮች የብቁነት ክፍልን ይመልከቱ)።
- እንዲሁም ሰራተኞች $0 መክፈል ወይም በወርሃዊ ፕሪሚየሞች ቅናሽ ማግኘት ይችላሉ።
- አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው ብዙ የጤና መድን እቅዶችን ማቅረብ ሊመርጡ ይችላሉ። በአነስተኛ የንግድ ገበያችን
- አማካኝነት እቅዶች በብር፣ በወርቅ ወይም በፕላቲኒየም ደረጃዎች ቀርበዋል።
- ወጪዎችን በመክፈል ረገድ ምን ያህል ለጋስ እንደሆኑ ለማመልከት በ HC4CC ውስጥ ያሉ እቅዶች ከ3 የብረት ደረጃዎች በአንዱ ተመድበዋል። የብረት ደረጃዎች ትኩረት የሚያደርጉት እቅዱ የህክምና ወጪዎችን ለመክፈል የሚጠበቅበት ነገር ላይ ብቻ ሲሆን የሚሰጠውን የጤና እንክባክቤ ጥራት ግምት ውስጥ አያስገባም።
ፕላቲኒየም90%ወርቅ80%ብር70%
- በአጠቃላይ የብር እቅዶች ዝቅተኛ ፕሪሚየሞች አሏቸው ነገር ግን ሰራተኞቹ የተሸፈኑ አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ጊዜ ተጨማሪ ይከፍላሉ።
- በአጠቃላይ የወርቅ እና የፕላቲኒየም እቅዶች ከፍተኛ ፕሪሚየሞች አሏቸው ነገር ግን ሰራተኞች የተሸፈኑ አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ጊዜ አነስተኛ ክፍያ ይከፍላሉ።
- ወጪዎችን በመክፈል ረገድ ምን ያህል ለጋስ እንደሆኑ ለማመልከት በ HC4CC ውስጥ ያሉ እቅዶች ከ3 የብረት ደረጃዎች በአንዱ ተመድበዋል። የብረት ደረጃዎች ትኩረት የሚያደርጉት እቅዱ የህክምና ወጪዎችን ለመክፈል የሚጠበቅበት ነገር ላይ ብቻ ሲሆን የሚሰጠውን የጤና እንክባክቤ ጥራት ግምት ውስጥ አያስገባም።
- ፕሪሚየሞች (ማንኛውም ካለ) በቀጥታ የሚከፈሉት ለDC Health Link ነው።
- ምንም እንኳን ሰራተኞች የተለያዩ የጤና መድን ኩባንያዎችን ቢመርጡም፣ አንድ ቀጣሪ መክፈል ያለበት አንድ ክፍያ ብቻ ነው።
- የመስመር ላይ ክፍያን ጨምሮ በርካታ የክፍያ ዘዴዎች አሉ።
- አሰሪዎች (ምንም እንኳን ግዴታ ባይሆኑም) ለሰራተኞቻቸው ወርሃዊ ፕሪሚየሞች እንዲያዋጡ ይበረታታሉ።
- በHC4CC የሰለጠኑ ባለሙያዎች አሰሪዎችን እና ሰራተኞቻቸውን በምዝገባ ሂደት የሚያግዙ ይሆናል።
ብቁነት፦ የልጅ እድገት ማዕከል ወይም ቤት አገልግሎት አቅራቢ በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ የተመሰረተ መሆን አለበት። ሁሉም ሰራተኞች የዲስትሪክት ነዋሪ ሆኑም አልሆኑም ብቁ ናቸው። የሰራተኞች ብዛት ከ100 የሙሉ ጊዜ ሰራተኞች (FTEs) መብለጥ የለበትም እንዲሁም አስተዳደራዊ እና ፈቃድ ያልተሰጣቸውን አስተማሪዎች ሊያካትት ይችላል።
- የሙሉ- ወይም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች የሆኑ የዲስትሪክቱ ነዋሪዎች (እና ቤተሰቦቻቸው) በግል እና በቤተሰብ የገበያ ቦታችን ለመመዝገብ ለነጻ ፕሪሚየሞች ብቁ ናቸው ( የዲሲ ነዋሪ ሰራተኛ ክፍላችንን ይመልከቱ)።
- የዲስትሪክት ነዋሪዎች ያልሆኑ ሰዎች በአነስተኛ የንግድ የገበያ ቦታችን በኩል ለነጻ ወይም ዝቅተኛ ወጭ ላላቸው ፕሪሚየሞች ብቁ ናቸው።
ነጻ የጤና መድህን፦ አንድ አሰሪ የKaiser Permanente KP DC Essential Gold 500/25/20%/Vision ን እንደ ማጣቀሻ እቅዱ ለማቅረብ ከመረጠ እና ሰራተኞች ይህንን እቅድ ከመረጡ፣ ሁለቱም አሰሪው እና ሰራተኞቹ ለፕሪሚየሞች $0 ይከፍላሉ።
ነጻ ወይም ዝቅተኛ ፕሪሚየሞች የ12 ወራት ዋስትና አላቸው።
በ DC Health Link ላይ የተዘጋጁትን የ2025 የአነስተኛ የንግድ ስራ የጤና እና የጥርስ ህክምና እቅዶች * አግኝተው ያወዳድሩ።
* አሰሪው ዝቅተኛ ወጪ ያለው የጥርስ ህክምና እቅዶችን ሊያቀርብ ይችላል፣ ነገር ግን እነዚያ እቅዶች ለHC4CC ፕሪሚየም ቅናሽ ብቁ አይሆኑም።
ጃኗሪ 1፣ 2025 የሚጀምሩ የሽፋን ቀነገደቦች
አሰሪዎች፦ ዲሴምበር 5፣ 2024
የDC Health Link መለያ ይፍጠሩ፣ የሰራተኛ ዝርዝር ያቅርቡ እና የጥቅም ጥቅል ያጠናቅቁ
ማስታወሻ፦ የDC Health Link ሰራተኞች እንደ አሰሪ ይህንን ያደርጉልዎታል (ወይም ከአሰሪው ደላላ ጋር የሚሰሩ ይሆናል) ነገር ግን ከDC Health Link ሰራተኞች ጋር ቀጠሮ መያዝ
የፕሪሚየም ክፍያ፦ ዲሴምበር 12፣ 2024
የሰራተኛ እና/ወይም የአሰሪ ድርሻ ለDC Health Link (የሚመለከተው ከሆነ) ይከፈላል። አሰሪዎች እና ሰራተኞች የነፃ ሽፋን ምርጫን ከመረጡ፣ ምንም ክፍያ አይከፈልም።
ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ ይህንን የእውቂያ ቅጽ ይሙሉ (formulario en español) ከቡድናችን ተጨማሪ እገዛ ለማግኘት።