የጤና ኢንሹራንስ አጠቃላይ እይታ

የዲሲ ሄልዝ ሊንክ DC Health Link ለዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪዎች፣ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ለሚገኙ የአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች እና ሠራተኞቻቸው ጥራት ያለው ተመጣጣኝ የጤና ኢንሹራንስ ያቀርባል። አማርኛ የሚናገሩ የሠለጠኑ የባለሙያዎች ቡድን አለን፤ እንዲሁም የእርስዎን ፍላጎት እና በጀት የሚያሟላ የጤና ኢንሽራንስ እንዲያገኙ ለማገዝ ዝግጁ ነን።

ምን ዓይነት የጤና ኢንሹራንስ ነው የሚፈልጉት?

ለጤና ኢንሹራንስ ለመክፈል እርዳታ ማግኘት እችላለሁን?

አዎ። ለጤና ኢንሹራንስ ለመክፈል እርዳታ ማግኘት እንዲችሉ፤ ለገንዘብ እርዳታ ፕሮግራም ብቁ መሆን ይኖርብዎታል። ብቁ መሆንዎትን ለማየት ማመልከቻ ማስገባት አለብዎት። በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል ለሚከተሉት ፕሮግራሞች ማመልከት ይችላሉ፦

ሜዲኬድ - ሜዲኬድ ዝቅተኛ ገቢ እና / ወይም የአካል ጉዳተኛ ለሆኑ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የጤና አገልግሎት ሽፋን የሚሰጥ የጤና ኢንሹራንስ ፕሮግራም ነው። ሜዲኬድ፤ የሐኪም ጉብኝትን፣ የሆስፒታል እንክብካቤን፣ መድሃኒትን፣ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶችን፣ ትራንስፖርትን እና ሌሎች ብዙ አገልግሎቶችን ይሸፍናል። የሜዲኬድ ሽፋን ለማግኘት በዓመቱ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ማመልከት ይችላሉ።

የግል የጤና ኢንሹራንስ የታክስ ክሬዲቶች እና የወጪ-መጋራት ቅናሾች - ለሜዲኬይድ ብቁ ካልሆኑ ነገር ግን የእርስዎ ገቢ ዝቅተኛ ከሆነ እና የተወሰኑ ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ፤ የግል ኢንሹራንስ ፕላን ለመግዛት የሚያግዝዎት የታክስ ክሬዲቶች (tax credits) እና / ወይም ሲልቨር ፕላን ከመረጡ ከኪስዎ- የሚከፈሉ ወጪዎችን ዝቅ ለሚያደርግልዎት የወጪ-መጋራት ቅናሾች (cost-sharing reductions) ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

በራሴ ቋንቋ እርዳታ ማግኘት እችላለሁን?

አዎ። እርስዎ ወይም እርስዎ እየረዱዋቸው ያሉ ሰው በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል ሽፋን የማግኘት ብቁነትን አስመልክቶ ጥያቄ ካላችሁ ያለ ምንም ወጪ በአማርኛ እርዳታ እና መረጃ የማግኘት መብት አላችሁ። ከአስተርጓሚ ጋር ለመነጋገር በስልክ ቁጥር (855) 532-5465 ይደውሉ። እባክዎን መስመር ላይ እንዳሉ በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት በስልክዎ ላይ የትኛውን ቁጥር መጫን እንዳለብዎት የሚነግርዎት መልዕክት በአማርኛ እስከሚመጣ ይጠብቁ። ሽፋን ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ፤ ስለ አከፋፈል፣ ወይም የትኛው ሽፋን እንዳለው ለመጠየቅ የጤና ኢንሽራንስ ኩባኒያዎን በኢንሹራንስዎ ካርድ ወይም የወርሃዊ ክፍያ መጠየቂያ ላይ ብሉት የስልክ ቁጥሮች ማነጋገር ይኖርብዎታል። ሜዲኬድ ውስጥ የተመዘገቡ ከሆነ በ (800) 620-7802 ይደውሉ።

በአማርኛ ሌላ ምን ጠቃሚ መረጃ ማግኘት ይቻላል?

በአማርኛ የሚገኙ የማመልከቻ ቅጾች፣ የተጠቃሚ መመሪያዎች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ከታች ተዘርዝረዋል፤ እንዲሁም በፒዲኤፍ ፎርማት ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል።

ለጤና ሽፋን ማመልከቻ
ግለሰቦች እና ቤተሰቦች መቆጣጠሪያ ዝርዝር
2017 “ሁለተኛው ዝቅተኛው ወጪ ሲልቨር ፕላን”
ነጻ ለመሆን (ለኤግዘምፕሽን) ማመልከቻ
ለግል/ለቤተሰብ የጤና ሽፋን የይግባኝ መጠየቂያ
individual and family
(855) 532-5465 / TTY: 711 ስልክ ደውለው በአማርኛ እርዳታ ለማግኘት ከፈለጎ፤ መስመር ላይ እንዳሉ በስልክዎ ላይ የትኛውን ቁጥር መጫንእንዳለብዎት የሚነግርዎት መልዕክት እስከሚመጣ ይጠብቁ።
የንግድ ድርጅቴ ብቁ ነውን?

የአነስተኛ ንግድ ድርጅት ባለቤቶች ለሠራተኞቻቸው ጥራት ያለው የጤና ኢንሹራንስ ሲያቀርቡ በሥራ ገበያ ውስጥ ጥሩ ተፎካካሪ እንድሚያደርጎት ያውቃሉ። የዲሲ ሄልዝ ሊንክ (DC Health Link) ከ1-50 ሰራተኞች ያሉዋቸውን የአነስተኛ ንግድ ድርጅቶችን ያገለግላል። የንግድ ድርጅትዎ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የሚገኘው \ከሆነ እና አንድ ሙሉ ሰዓት ይሚሥራ ቋሚ ሰራተኛ ካልዎት (ባለቤቶን፣ወይም የቤተሰብ አባላትን ሳይጨምር) የዲሲ ሄልዝ ሊንክ ላይ የጤና ጥቅሞች ፕሮግራም መፍጠር ይችላሉ። ምንም ሰራተኞች ሳይኖርዎት የግል ተዳደሪ ከሆኑ የግል እና የቤተሰብ የጤና ኢንሹራንስ ለማግኘት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ምን ዓይነት የጤና ኢንሹራንስ ማግኘት ይቻላል?

የዲሲ ሄልዝ ሊንክ ለዋሽንግተን ዲሲ አገልግሎት ከሚያቀርቡ ዋና የጤና ኢንሹራንስ ኩባኒያዎች ከ100 በላይ የጤና ኢንሹራንስ ፕላኖችን ያቀርባል። ሁሉም ፕላኖች ቢያንስ በሕግ የሚጠየቁትን ዋና ዋና የጤና አገልግሎቶች እንዲሁም የተወሰኑ መሰረታዊ ጤና መከላከያ አገልግሎቶችን ያካትታሉ። ሁሉም ኢንሹራንስ ኩባኒያዎች የሚሰጡዋቸውን ጥቅሞች እና ዋጋዎች ማሳወቅ ስላለባቸው፤ በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል የሚገኙት የፕላኖች በዋጋም ጥራት በጣም ተወዳዳሪ ። በተጨማሪም የዲሲ ሄልዝ ሊንክ ለአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች የተለያዩ የጥርስ ኢንሹራንስ ፕላኖች ያቀርባል።

ምን ያህል ያስከፍላል?

የዲሲ ሄልዝ ሊንክ ለሠራተኞችዎ እና በስራቸው ላሉ ጥገኞች የጤና ኢንሹራንስ ወርሃዊ ፕሪሚየም ወጪ ምን ያህል አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለብዎት እንዲወስኑ ያስችልዎታል። ለእያንዳንዱ ብቁ ለሆነ ሠራተኛ ወጪ ቢያንስ 50 በመቶ አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርብዎታል። ለቤተሰብ አባላትም የጤና ኢንሹራንስ ማቅረብ ይችላሉ እንዲሁም ለወርሃዊ ፕሪሚየማቸው አስተዋጽኦ ማድረግ ወይም አለማድረግ የራስዎ ውሳኔ ነው። በሚያቀርቡት ዝቅተኛ የዋጋ ፕላን ለእያንዳንዱ ሠራተኛ 50 በመቶ አስተዋጽኦ ለማድረግ አቅም ከሌልዎት በዓመታዊው ኢንሹራንስ ምዝገባ ወቅት ለወጪዎች ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ለማድረግ ወይም ምንም አስተዋጽኦ ላለማድረግ መምረጥ ይችላሉ። የጤና ኢንሹራንስ ፕሪሚየም ወጪዎች በእያንዳንዱ ሽፋን ባለው ሰው ዕድሜ ላይ የተመሠረቱ ናቸው።

የንግድ ድርጅቴ መመዝገብ የሚችለው መቼ ነው?

የአነስተኛ ንግድ ድርጅቶች የዲሲ ሄልዝ ሊንክ ላይ በዓመት ውስጥ በማንኛውም ጊዜ የጤና ጥቅሞች ፕሮግራም መፍጠር ይችላሉ፤ እንዲሁም በዓመቱ በተመሳሳይ ጊዜ ፕላኖቻቸውን ያድሳሉ።

እንዴት ነው ሠራተኞች ለጤና ኢንሹራንስ መመዝገብ የሚችሉት?

አሠሪዎ በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል የጤና ጥቅሞች ፕሮግራም የሚያቀርቡ ከሆነ፤ አሠሪዎ መቼ እና እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎት ይነግርዎታል። አሠሪዎን ይጠይቁ። አሠሪዎ በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል የጤና ኢንሹራንስ የማያቀርቡ ከሆነ፤ የግል እና የቤተሰብ የጤና ኢንሹራንስ ለመግዛት ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የንግድ ድርጅቴ ለጤና ኢንሹራንስ ክፍያ እርዳታ ማግኘት ይችላልን?

ከ25 ቋሚ ሠራተኞች በታች ያላቸው አነስተኛ ንግድ ድርጅቶች ለfederal tax credits (የፌዴራል ታክስ ክሬዲት) ብቁ በመሆን ወጪዎቻቸውን ዝቅ ማድረግ ይችሉ ይሆናል። የታክስ ክሬዲቱ የአሠሪ አስተዋጽኦ እስከ 50 በመቶ ይሸፍናል (ወይም ለትርፍ ለማይሠራ ድርጅት እስከ 35 በመቶ) ብቁ ለመሆን የንግድ ድርጅትዎ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርበታል፦ ከ 25 የሙሉ ጊዜ ቋሚ ሠራተኞች በታች ያለው፣ የሠራተኛ ደሞዝ በአማካይ ከ በዓመት ከ$50,000 በታች የሆነ፣ በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል የጤና ኢንሹራንስ የገዛ፣ እንዲሁም የእያንዳንዱን ብቁ ሠራተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን ወጪ ቢያንስ 50% የሚከፍል።

የአስተርጓሚ ወይም የባለሙያ እርዳታ ማግኘት እችላለሁን?

አዎ። የዲሲ ሄልዝ ሊንክን አስመልክቶ ጥያቄ ካለዎት ያለ ምንም ወጪ በአማርኛ እርዳታ እና መረጃ የማግኘት መብት አለዎት። ከአስተርጓሚ ጋር ለመነጋገር በስልክ ቁጥር (855) 532-5465 ይደውሉ። እባክዎን መስመር ላይ እንዳሉ በቋንቋዎ እርዳታ ለማግኘት በስልክዎ ላይ የትኛውን ቁጥር መጫን እንዳለብዎት የሚነግርዎት መልዕክት በአማርኛ እስከሚመጣ ይጠብቁ። አስተርጓሚውም ከእርስዎ ምንም ወጪ ሳይደረግ የጤና ጥቅሞች ፕሮግራምዎን ለማዘጋጀት እና ከፍላጎትዎ እና ከበጀትዎ በተሻለ የሚስማሙ ፕላኖችን በመምረጥ የሚያግዝዎት ባለሙያ የኢንሽራንስ አስማሚ ጋር እንዲገናኙ ይረዱዎታል። በተጨማሪም ለሠራተኞችዎ ያለምንም ክፍያ እርዳታ የሚሰጡ አስማሚዎችም አሉ።

በአማርኛ ሌላ ምን ጠቃሚ መረጃ ማግኘት ይቻላል?

በአማርኛ የሚገኙ የማመልከቻ ቅጾች፣ የተጠቃሚ መመሪያዎች እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎች ከታች ተዘርዝረዋል፤ እንዲሁም በፒዲኤፍ ፎርማት ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል።

አዲስ ቀጣሪዎች በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል የጤና ሽፋን እንዴት ማቅረብ እንደሚችሉ
አዲስ ተቀጣሪዎች - በዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል ለጤና ሽፋን እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል
የጤና ሽፋኖንበዲሲ ሄልዝ ሊንክ በኩል ማሳደስ
የተቀጣሪዎን ዝርዝር(ሮስተር)
ለተቀጣሪ ማሳደሻ ክፍት ምዝገባ የዲሲ ሄልዝ ሊንክ መምሪያ(ጋይድ)
small business
(855) 532-5465 / TTY: 711 ስልክ ደውለው በአማርኛ እርዳታ ለማግኘት ከፈለጎ፤ መስመር ላይ እንዳሉ በስልክዎ ላይ የትኛውን ቁጥር መጫንእንዳለብዎት የሚነግርዎት መልዕክት እስከሚመጣ ይጠብቁ።