በDC Health Link አማካኝነት HealthCare4ChildCare፦
ለቅድመ ልጅነት ትምህርት አቅራቢዎች እና ቡድኖቻቸው ተመጣጣኝ የሆነ የጤና ሽፋን
በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ላሉ የልጅ እድገት ማዕከላት ወይም ቤቶች ሰራተኞች HealthCare4ChildCare
HealthCare4ChildCare (HC4CC) በዲሲ ኦፊስ ኦፍ ዚ ስቴት ሱፐርኢንተንደንት ኦፍ ኤጁኬሽን-ፈቃድ ለተሰጣቸው የቅድመ ልጅነት እድገት ማዕከላት እና ቤቶች ውስጥ ላሉ ሰራተኞች በDC Health Link በኩል ነጻ ወይም ዝቅተኛ ወጭ ያለው የጤና መድን ይሰጣል።
ብቁነት፦ የዲሲ ነዋሪ ያልሆኑ ሰራተኞች ተሳትፎ ዲሲን መሰረት ባደረገ የልጅ እንክብካቤ ማዕከላቸው ወይም የቤት አቅራቢ ቀጣሪያቸው በHC4CC ውስጥ በመመዝገቡ ላይ የሚወሰን ነው።
ማስታወሻ፦ የHC4CC ፕሪሚየም ቅናሽ ለጥገኞች አልተዘጋጀም።
ነጻ ወይም ዝቅተኛ ፕሪሚየሞች የ12 ወራት ዋስትና አላቸው።
በDC Health Link ላይ የቀረቡትን የ2025 የአነስተኛ የንግድ ስራ የጤና እና የጥርስ ህክምና እቅዶች* አግኝተው ያነጻጽሩ።
*ቀጣሪዎ ዝቅተኛ ወጪ ያለው የጥርስ ህክምና እቅዶችን ሊያቀርብ ይችላል፣ ነገር ግን እነዚያ እቅዶች ለHC4CC ፕሪሚየም ቅናሽ ብቁ አይደሉም።
ጃኗሪ 1፣ 2025 የሚጀምሩ የሽፋን ቀነገደቦች
ሰራተኞች፦ ዲሴምበር 10፣ 2024 ክፍት ምዝገባ ያበቃል
ሰራተኞች በእቅድ ውስጥ መርጠው ይመዘገባሉ
ማስታወሻ፦ DC Health Link የሚያግዝዎ ይሆናል (ወይም ከአሰሪዎ ወይም ከደላላዎ ጋር ይሰራል)
ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎ ይህንን የእውቂያ ቅጽ ይሙሉ (formulario en español) ከቡድናችን ተጨማሪ እገዛ ለማግኘት።